ብሩህ 2014

ብሩህ የስራ የፈጠራ የሃገሪቷን ቁልፍ ችግሮችን ለመፈታት አዳዲስ ሃሳቦችን የሚያፈልቁና ስራ የሚፈጥሩ ወጣቶችን ለማበረታታት የተዘጋጀ ዓመታዊ የውድድር ፕሮግራም ነው። ይህ ውድድር አመርቂ የንግድ ሃሳብ ይዘው ለመጡ ወጣቶች የስልጣና፣ የመነሻ ገንዘብና የንግድ ማብቂያ ድጋፍ በመስጠት አትራፊ፣ ለወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥሩ እንዲሁም ለሌች ተምሳሌት የሚሆኑ ወጣቶችን መፍጠር ዋና አላማው ነው።

ሁለተኛው የብሩህ ሃገር አቀፍ ውድድር ለምዝገባ ክፍት ሆኗል

የማመልከቻ ቀን መስከረም 5፣2014ዓ.ም ይጀምራል

በአማረኛ ለማመልከት ይሄን ቁልፍ ይጫኑ

ብሩህ 2014 በቅርብ ቀን ይጠብቁ

ልቀት የሃገሪቷን ቁልፍ ችግሮችን ለመፈታት አዳዲስ ሃሳቦችን የሚያፈልቁና ስራ የሚፈጥሩ ወጣቶችን ለማበረታታት የተዘጋጀ አመታዊ የውድድር ፕሮግራም ነው። ይህ ውድድር አመርቂ የቢዝነስ ሃሳብ ይዘው ለመጡ ወጣቶች የስልጣና፣ የመነሻ ገንዘብና የቢዝነስ ማብቂያ ድጋፍ በመስጠት አትራፊ፣ ለወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥሩ እንዲሁም ለሌች ተምሳሌት የሚሆኑ ወጣቶችን መፍጠር ዋና አላማው ነው።

የ2013 ውድድር


50

Entrepreneurs

ማሰልጠን

50 የተመረጡ የቢዝነስ ሃሳቦች ለአንድ ወር የስራ ፈጠራ ስልጠና ይወስዳሉ

20

Finalists

መሸለም

20 በውድድሩ ጥሩ ውጤት ያመጡ የቢዝነስ ሃሳቦች የመነሻ ገንዘብ ይሸለማሉ

10

Entrepreneurs

ማብቃት

10 ከፍተኛ ውጤት ላመጡ የስራ ሃሳቦች የስድስት ወር የቢዝነስ ማፋጠኛ ድጋፍ ያገኛሉ

ማን ማመልከት ይችላል?

  • የንግድ / ሀሳብ መስራቾች ኢትዮጵያዊያን ወይም የስራ ፈቃድ ያላቸው ስደተኞች መሆን አለባቸው
  • ንግዶች በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲፈፀሙ መታቀድ አለበት
  • አመልካቾች ከ15-29 ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ መሆን አለባቸው
  • የተመዘገበ ንግድ ከሆነ ንግዱ ከ 2 ዓመት በላይ መሆን የለበትም

እንዴት ማመልከት ይቻላል?

ለብሩህ 2013 ለማመልከት የደረጃ በደረጃ መመሪያ
በድህረ ገጽ ለማመልከት
  1. ከዚህ በላይ ያለውን የማመልከቻ ቁልፍ በመጫን ይጀምሩ
  2. የጉግልፎርሙን ያጠናቅቁ
  3. አስፈላጊሰነዶችዎን ያስገቡ
በአካል ለማመልከት
  1. በስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት በመምጣት የማመልከቻ ቅጽ መውሰድ
  2. የማመልከቻ ቅጹን መሙላት
  3. የተሞላውንቅጽ ከአስፈላጊ ሰነዶች ጋር በማያያዝ ለስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት ማስረከብ
  4. ይኼውነው!

የውድድሩ ሂደት

ማመልከት

አመልካቾች በድህረገፁ ላይ በሚገኘው ማመልካቻ ቅፅ ተጠቅመው ወይንም በስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ዋና ቢሮ በመምጣት ያመለክታሉ

ማጣሪያ

አመልካቾች ለውድድሩ በተዘጋጅው የማጣሪያ መስፈርት ይመረጣሉ

ስልጠና

50 የተመረጡ አመልካቾች የአንድ ወር የአንተርፕርነር ስልጠና ይወስዳሉ

ውድድር

የሰለጠኑት አመልካቾች በዳኞች ፊት ቀርበው ይወዳደራሉ

ሽልማት

20 በውድድሩ ጥሩ ውጤት ያመጡ የገንዘብ ሽልማት ያገኛሉ

ማብቃት

10 በውድድሩ ምርጥ ውጤት ያመጡ የስድስት ወር የቢዝነስ ማፋጠኛ ድጋፍ ያገኛሉ